በአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/201...

image description
- In code inforcement    0

በአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ ።

በአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ ።

            መስከረም 19/2019 ዓ.ም
                 አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ከከተማው ለተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል ።

​በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለጹት ህብረተሰቡን በማሳተፈና በቅንጅት ስራዎች በመሰራታቸው በከተማችን የሚፈጸሙ የደንብ መተላለፎች በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ችለዋል።

ቅጣት ላይ ከመገባቱ በፊት ህብረተሰቡ ስለ ደንብ ማስከበር አዋጆችና መመሪያዎች በቂ ግንዛቤ አግኝቶ፣ የደንብ መተላለፎችን በጋራ የሚከላከልበትንና ለከተማዋ ውበትና ጸጥታ አጋዥ የሚሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸት ተገቢ መሆኑን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

​በመድረኩ በአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 ዙሪያ የተዘጋጀውን ሰነድ በባለስልጣኑ የደንብ ስርጸትና ግንዛቤ ማስጨበጫ ቡድን መሪ አቶ ደመረ በለጠ የቀረበ ሲሆን፤ በሰነዱም ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የአደጋ ስጋት ቅነሳ አመለካከት አቅጣጫዎች፣ የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብና መመሪያ አስፈላጊነት፣ የደንብ ቁጥር 132/2014 ይዘትና በአተገባበሩ ላይ የባለድርሻ አካላት ድርሻ በዝርዝር ቀርቧል።

​ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ ለወደፊቱም ህግና ደንብን በማስከበር ረገድ ቅንጅታዊ አሰራሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments