ባለስልጣኑ በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካማ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቱ አስረከበ፡፡

ባለስልጣኑ በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካማ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቱ አስረከበ

                03 - 04 - 2017 ዓ.ም
               ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በስሩ የሚገኙ ወረዳዎችን በማስተባበር በክፍለ ከተማው ወረዳ 10 አቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቱ አስረክቧል ። 

በርክክብ ፕሮግራሙ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ ደንብ መተላለፎችንና ህገ-ወጥ ተግባራትን ከመከላከል ጎን ለጎን ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ ችግር ፈቺ የሆኑ ሰው ተኮር የበጎፍቃድ ስራዎችን በመስራት ለህብረተሰቡ ያለውን አለኝታነት በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።

አክለውም ይህ  ሰው ተኮር በጎ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ  እንደሚቀጥል ተናግረዋል። 

የቂርቆስ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ዳኜ ሂርጳሳ በበጀት ዓመቱ ከተያዙት እቅዶች ውስጥ የተሰጠንን ተልዕኮ ከማሳካት በሻገር በተለያዩ  የበጎ ፈቃድ ተግባራት መሳተፋቸውን ገልፀው በክ/ከተማው ወረዳ 10 የአመራሩን እና የኦፊሰሩ የጉልበት ወጪን ሳይካተት ከስድስት መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ በሶስት ሳምንት ውስጥ ቤቱን ገንብተው ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል ። 

ደንብ ማስከበር ህገ-ወጥነትን ከመከላከል ጎን ለጎን ኦፊሰሩን በማስተባበር በሰው ተኮር ስራ ላይ በመሳተፍ ላከናወኑት የአቅመ ደካማ ቤት ማደስ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ የሰውሀረግ ገልጸዋል ። 

የቤት እድሳት የተደረገላቸው ወ/ሮ ዙሪያሽወርቅ ግዛው በተደረገላቸው በጎ ተግባር መደሰታቸውን በመግለፅ በተግባሩ ለተሳተፉ በሙሉ ላቅ ያለ ምሳጋና አቅርበዋል። 

በእለቱ የቤት ግንባታው ሲከናወን ድጋፍ ላደረጉ እና ለአስተባበሩ አካላት የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል ። 

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments