
ባለስልጣኑ ስራዎቹን በድህረ-ገጽ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና ሰጠ
ባለስልጣኑ ስራዎቹን በድህረ-ገጽ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና ሰጠ
04 - 04 - 2017 ዓ.ም
**** አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሚያከናውናቸውን ስራዎች በኮሙዪኒኬሽን አግባብ ተደራሽ ለማድረግ ከክፍለ ከተማ እስከ ከወረዳ ላሉ የኮሙኒኬሽን ፎካል ፐርሰኖች/ተወካዮች/ ስልጠና ሰጠ።
በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ተቋሙ የሚያከናውናቸውን አጠቃላይ ስራዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ከተቋሙ ጎን መሰለፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላቀች ሀይሌ ዘመኑ የኤሌትሮኒክስ ሚዲያ እና ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም መረጃዎችን በፈጣን መንገድ ለሚፈለገው አካል ለማስተላለፍ ምቹ ሁኔታዎችንመፈጠሩ ገልፀዋል
የመረጃ ቅብብሎሽና ግንዛቤ ለመፍጠር ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ስልጠናው በአግባቡ እንዲከታተሉ አስገንዝበዋል ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ሚሊዮን ካሳሁን ስለ ድህረገጽ (Website)ምንነት ፣ ጥቅምና ጉዳት እና ባለስልጣኑ አዲስ የከፈተውን የራሱን ድህረ ገጽ አጠቃቀም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ስጥተዋል።
በስልጠናው ስለተቋሙ የሚያከናውነው ተግባራት ለማወቅ ሀሳብና አስተያየት ለመስጠት በቀላሉ http://www.aacea.gov.et መጠቀም እንደሚቻል ተገልጿል ።
በእለቱ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች በ2017 በጀት አመት በ4 ወር የተከናወኑ የኮሙዩኒኬሽን ስራዎችን በተመለከተ የተደረገው የድጋፍና ክትትል ሪፖርት በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ ወ/ሮ ኤደን በዳሶ ቀርቧል።
በሪፖርቱ በክፍለ ከተሞቹ የታዩ ጠንካራ ጎኖች፣ የታዪ ክፍተቶች እንዲሁም በቀጣይ መስተካከል የሚገባቸው ተግባራት ቀርበዋል።
በእለቱ በተግባቦትና በሶሻል ሚዲያ ዜናዎች ባህሪያት፣ በመሰረታዊ የዜና አጻጻፍና በቀጣይ የስራ ግንኙነቶች በተመለከተ በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ የምስርች ግርማ ገለፃ ተደርጓል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments