በባለስልጣኑ በስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ እ...

image description
- In code inforcement    0

በባለስልጣኑ በስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎቹን ተገመገመ

የባለስልጣኑ በስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎቹን ተገመገመ 

                04 - 04 - 2017 ዓ.ም
                    አዲስ አበባ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችን ከማዕከል ዳይሬክተሮች እና የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎች ጋር በጋራ በመሆን የግምገማ መድረክ አካሂዷል ። 

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ኮ/ር አህመድ መሐመድ የተሰሩ ሰራዎችን የጋራ ማድረግ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ለቀጣይ የተሻለ ሰራ ለማከናወንና ጥሩ ውጤት ለማምጣት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

አክለውም የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል እንዲሁም የተከናወኑ ተግባራትን መረጃን በአግባቡ ማስቀመጥና በሚፈለጉበት ጊዜ ለማሳየት ዝግጁ ማድረግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ። 

የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የደንብ መተላለፍ መከላከል ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት የህዳር ወር ሪፖርት እና ለክፍለ ከተማዎች ያከናወነውን የድጋፍና ክትትል ሪፖርት በባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ ድጋፍና ክትትል ቡድን መሪ ወ/ሪት አልማዝ በቀለ ቀርቧል። 

በስራ አፈጻጸም የነበሩትን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል የነበሩንን ደካማ ጎኖች በመቅረፍ የክ/ከተሞችን የመፈጸም አቅም በማሳደግና ህገወጥ ተግባራትን በመከላከል ከተማችን ደንብ ጥሰት የቀነሰባት ጽዱ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ ወቅቱን የጠበቀ ግምገማ ማካሄድ አስፈላጊ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል ። 

የስልጠና እና ጥናት ዳይሬክቶሬት በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ሰራዎች አጭር ሪፖርት በስልጠና ቡድን መሪ አቶ አባይነህ ጥጋቡ አቅርበዋል ። 

በቀረቡት ሪፖርት ዙርያ ውይይት የተደረገ ሲሆን የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ተነስተው ከተቋሙ ሀላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ የዘርፋ ኃላፊ አስቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል፡፡ 

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments