ባለስልጣኑ የአመራሩን እውቀት ለመገንባት እየሰራ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የአመራሩን እውቀት ለመገንባት እየሰራ መሆኑ ገለፀ

"የአመራሩን እውቀት ለመገንባት እየተሰራ ነው"

             06/04/2017 ዓ.ም
             ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከማዕከል  እስከ ወረዳ ኃላፊዎችእና ለማዕከሉ ዳይሬክተሮች ስትራቴጂካል መሪ ለማድረግ  የአቅም ግንባታ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠና እና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር አህመድ መሀመድ ተናገሩ።

ባለስልጣኑ ፒያሳ በሚገኘው በተቋሙ መስሪያ ቤት በትላንትናው ዕለት የተጀመረው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬ ውሎው የለውጥ እና የውጤታማ አመራር  ውሳኔ ሰጪነትን የተመለከቱ ርዕሶችን ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ከኢትዮጲያ ስራ አመራር ኢንሰቲትዩት በተጋበዙ ዶ/ር ጀቤሳ ተሾመ እና በአቶ ሀገር መኩሪያ  እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና በነገው ዕለት የሚጠናቀቅ ሲሆን በቀጣይም የአመራሩን እውቀትና ክህሎት የላቀ ለማድረግ እንደሚሰራ የዘርፍ ኃላፊው አስታውሰዋል። 

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments