
በስልጠናው የተገኘውን እውቀት ተግባር ላይ ማዋል እንደሚገባ ተገለፀ።
በስልጠናው የተገኘውን እውቀት ተግባር ላይ ማዋል እንደሚገባ ተገለፀ።
07/04/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ላሉ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው ዕለት አጠናቋል።
በመድረኩም የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙበት ሲሆን ፤ ሠልጣኞችም በቆይታቸው በርካታ ዕውቀቶችን የቀሰሙበት፤ በስራቸው ላይም የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያግዝ በመሆኑ ተቋሙ ላይ አውንታዊ ለውጥ የሚያመጣ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የደንብ ማስከበር ባለስልጣንም የአመራሩን ክህሎት በማሳደግ የተገልጋይ ህብረተሰቡን ለማርካታ የሄደበት ርቀት የሚደነቅና ስልጠናውንም ለሰጡት የኢትዮጽያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ ላይ ስር ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት በማሰብ በምንሰራው ስራ ላይ ከታች እስከ ላይ ያለው አመራርና ፈፃሚ የሚያሳየው ተሳትፎና ዝግጁነት ይበልጥ የሚያሰራና ተጨባጭ የሆነ ለውጥም ለማስመዝገብ የምናደርገውን ጉዞ እውን የሚያደርግ መሆኑን ገልፀው፤ እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎችም በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በስልጠና የተገኝውን እውቀት ቆራጥ አመራር በመሆን ወደ ተግባር መቀየር እና ተቋሙ በ2022 ዓ.ም ሊያሳካ ለወጠነው ራዕይው ሁሉም የበኩሉን አስተዋፆ እንዲያበረክት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘገባው:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments