ተቋሙ የበጎ ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል።

image description
- In code inforcement    0

ተቋሙ የበጎ ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል።

ተቋሙ የበጎ ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል።

09/04/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የበጎ ስራውን አጠናክሮ በማስቀጠል ለጌርጌሴኖን አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከአንድ መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አበረከተ።

ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ እንዲያስፈፅም ከተሰጠው ተልዕኮ በተጓዳኝ በርካታ በጎ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ሰብአዊ እና ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ የገለፁት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ናቸው።

በዛሬው ዕለትም ለጌርጌሴኖን አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከአንድ መቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አበርክቶ፤ በቀጣይም አቅም በፈቀደው ሁሉ እንደሚደግፉና ሠራተኛውም ማዕከሉን እንዲጎበኙ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ መለስ አየለ ለማዕከሉ በተደረገው ድጋፍ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን አመስግነው፤ ሁሉም ሠራተኛ ማዕከላቸውን መጥተው ቢጎበኙ ደስታቸው የላቀ እንደሆነ አስታውሰዋል።

አቶ መለስ አክለውም ከተማ አስተዳደሩ በሰጣቸው ሶስት ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የግንባታ መሰረት የተጀመረ ሲሆን ሁሉም ወገን 6860 ላይ OK በማለት የበኩሉን አስተዋፆኦ እንዲያበረክት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከዚህ ቀደም የመቄዶንያ አረጋውያን ማዕከል ሄዶ በመጎብኘት የአይነት ድጋፍ ማበርከት፣ ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅሩ 75  ህፃናትን መደገፍ፣ የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት ማደስ እና መገንባት፣ ደም መለገስ፣ ችግኝ ተክሎ መንከባከብ፣ የአርሶ አደሩን የደረሰ ሰብል ከማሳ ላይ መሰብሰብ እና ሌሎች ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ እየሠራ እንደሚገኝ ይታወሳል።

ዘገባው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments