
ባለስልጣኑ የበጎ ተግባር አገልግሎቱ በተለያዩ አገልግሎት ዘርፎች እየሰጠ ይገኛል።
ባለስልጣኑ የበጎ ተግባር አገልግሎቱ በተለያዩ አገልግሎት ዘርፎች እየሰጠ ይገኛል።
09/04/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በበጎ ተግባር ፕሮግራሙ ኦፊሰሮችን በማስተባበር በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አንቆርጫ ሠለም ሰፈር አካባቢ እገዛ የሚያስፈልጋቸው የሴት አርሶ አደር ለሆኑት ወ/ሮ አበቡ ባልቻ ሁለት ሄክታር የደረሰ ስንዴ እንዲሰበሰብ አደረገ።
ባለስልጣኑ ግለሰቧ በወረዳው በኩል ለተቋሙ ባደረጉት የእገዛ ጥሪ መሰረት ከ12 ወረዳዎች የተወጣጡ 120 ኦፊሰሮች በማስተባበር ሰብሉን በማጨድ፣ በመሰብሰብና በመከመር የደረሰውን ሰብል ወቅቴን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሽ ማድረግ መቻሉ የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅቤት ሀላፊ አቶ አያልነህ ካሳሁን ገልፀዋል።
አርሶ አደር ወ/ሮ አበቡ ባልቻ በተደረገላቸው እገዛ እጅግ መደሰታቸው ገልፀው ላገዙ ፣ላስተባበሩ እና ከተማው አስተዳደሩን በማመስገን እናታዊ ምርቃት ሰጥተዋል።
ባለስልጣኑ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ህገ ወጥ ተግባራት ከመከላከል ጎን ለጎን በችግር ጊዜ ለህብረተሰቡ ደራሽነቱ ያሳየበት መሆኑ ተገልጿል ።
ባለስልጣንኑ ከዚህ ቀደም የመቄዶንያ አረጋውያን ማዕከል እና ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ሄዶ በመጎብኘት የአይነት ድጋፍ ማበርከት፣ ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅሩ 75 ህፃናትን መደገፍ፣ የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት ማደስ እና መገንባት፣ ደም መለገስ፣ ችግኝ ተክሎ መንከባከብ፣ የአርሶ አደሩን የደረሰ ሰብል ከማሳ ላይ መሰብሰብ እና ሌሎች ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ እየሠራ እንደሚገኝ ይታወሳል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments