ባለስልጣኑ በህገ ወጥ መንገድ ጤንነቱን ያልተረጋ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በህገ ወጥ መንገድ ጤንነቱን ያልተረጋገጠ እንስሳት በማረድ ለህብረተሰቡ ሊያቀርብ የነበሩ ግለሰቦች መያዛቸውን ገለፀ

ባለስልጣኑ በህገ ወጥ መንገድ ጤንነቱን ያልተረጋገጠ እንስሳት በማረድ ለህብረተሰቡ ሊያቀርብ የነበሩ ግለሰቦች መያዛቸውን ገለፀ

                 ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም
                 ****አዲስ አበባ**** 

በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወሪዳ 02 ልዩ ቦታው ግራር አካባቢ በህገ ወጥ መንገድ ጤንነቱን ያልተረጋገጠ እንስሳት በማረድ ለህብረተሰቡ ሊያቀርብ የነበሩ ግለሰቦች በክፍለ ከተማና በወረዳው ደንብ ማስከበር አባላት በተደረገው ክትትል ከታረዱ እና ለእርድ ከተዘጋጁት እንስሳት ጋር መያዛቸው የወረዳው ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀለፊ አቶ ምህረቱ ደስታ ገልፀዋል ።

ድርጊቱ ሲፈፅምበት የነበረ ግለሰብ 15000/አስራ አምስት ሺህ/ ብር የተቀጣ ሲሆን በቦታው የተገኙ የታረደ የበግ ስጋ በማስወገድ ለህገ-ወጥ እርድ የተዘጋጁ 13 በጎች ለጠፍ በረት በማስረከብ ለመንግስት ገቢ ተደርገዋል።

ህገ ወጥ እርድ ጤንነቱን ያልተረጋገጠ እንስሳት እና ንፅህናውን ያልጠበቀ ስጋ  ስለሚቀርብ ለህብረተሰቡ ለጤና ጎጂ ከመሆኑ ባሻገር እንደህገር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት መሆኑ  የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙልጌታ ጎንፍ ገልፀዎል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments