
ባለስልጣኑ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤቱ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ሥራ አስጀመረ
ባለስልጣኑ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤቱ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ሥራ አስጀመረ
ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም
**** የአዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤቱ አስተባባሪነት በክፍለከተማው ወረዳ 14 የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት መርሃግብር በዛርው እለት አስጀምሯል።
መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ ኮማንደር አህመድ መሀመድን ጨምሮ የክፍለ ከተማው እና የወረዳ የደንብ ማስከበር አመራሮችና ኦፊሰሮች ተገኝተዋል።
በዕለቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ ኮማንደር አህመድ መሀመድ ከመደበኛ ስራችን በተጨማሪ በሰው ተኮር ተግባራት በንቃት በመሳተፍ የአቅመ ደካሞች ማዕድ በማጋራት፣የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበራት በመደገፍ፣ረዳት የሌላቸው የከተማው ነዋሪዎች ቤት በማደስ ባለስልጣኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ መሆኑ ገልፀዋል።
በመርሃ-ግብሩ የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ አለሙ መረዳዳትን፣ መደጋገፍንና አብሮነትን ባህል ለማድረግ በትብብር መስራት ይገባል የጀመርነውን የቤት እድሳት በፍጥነት አጠናቀን ለባለቤቱ እናስረክባለን ብለዋል።
ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
ዌብሳይት ገፃችን፦
https://www.aacea.gov.et/
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments