
ባለስልጣኑ በቀጣይ ስለሚሰሩ የሚዲያ ፕሮግራሞች ይዘት በተመለከተ ውይይት አካሄደ
ባለስልጣኑ በቀጣይ ስለሚሰሩ የሚዲያ ፕሮግራሞች ይዘት በተመለከተ ውይይት አካሄደ
15/04/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር በጋራ ለሚያዘጋጁት የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ፕሮግራሞች በተመለከተ በተሻለ ይዘትና አቀራረብ ለማዘጋጀት የባለስልጣኑ አመራሮች ፣የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ተወካዬች እና የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አባላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ውይይት ተካሄደ።
በውይይቱ የሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ዝግጅት እስታንዳርድ በተመለከተ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የቴሌቪዥን ዶክመንተሪ እና ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር አቶ ስንታየው ታደሰ የባለስልጣኑ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ይዘት እቅድ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
በውይይቱ የባለስልጣኑ ዋና ስራአስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል እና ህብረተሰቡ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የቴሌቪዥን ፕሮግራም ብዙ ህዝብ ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
አክለውም ፕሮግራሙ ማራኪ፣አዝናኝና፣አስተማሪ እና በማይሰለች መልኩ ሊቀርብ እንደሚገባና ለዚህም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
በውይይቱ የባለስልጣኑ ማኔጅመንት አባላት በቀረበው መነሻ ሀሳብ መሰረት በፕሮግራሙ መካተት የሚገባቸው ይዘቶች እንዲጨመር ሀሳብ ሠጥተዋል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments