በካይዘን ሳይንስ ትግበራ ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ።

image description
- In code inforcement    0

በካይዘን ሳይንስ ትግበራ ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ።

በካይዘን ሳይንስ ትግበራ ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ።
            
                 17/04 /2017ዓ.ም 
                ****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በካይዘን ትግበራ ንድፈ ሀሳብ ላይ ለተቋሙ ሰራተኞች በባለስልጣኑ የስብሰባ አዳራሽ ግንዛቤ ተፈጠረ::

የባለስልጣኑ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላቀች ሀይሌ የካይዘን አተገባበርን በተቋም ውስጥ መፈፀም ያለውን ፋይዳ በሙያው ልምድና እውቀት ካለው አሰልጣኝ ማግኘት ችግሮችን ለመቅረፍና ስራዎች ቀልጣፋ ለማድረግ አስተዋፆው የላቀ በመሆኑ ከስልጠናው የምናገኘውን እውቀት ወደተግባር ልንቀይር ይገባ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። 

ችግር ለሥራ መሻሻል ውድ ሀብት ነው ያሉት ስልጠናውን የሰጡት ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የካይዘን ንድፈ ሀሳብ አማካሪ የሆኑት አቶ ደፋር ቀፀላ ስለ ካይዘን ምንነት አተገባበርና ቀጣይነቱስ እንዴት ይጠበቅ በሚሉ እና ሌሎች አሳታፊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ስልጠናውን ሰተዋል::

በማጠቃለያውም ሰራተኞቹ ከስልጠናው ብዙ እውቀትን እዳገኙበት በመግለፅ፤ በቀጣይ ችግሮችን ከስልጠናው ባገኙት እውቀት በመነሳት ለመፍታትና የተሻለ ስራ ለመስራት መነሳሳትን እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል::

ዘገባ ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments