
"የሴት ጥቃት የኔም ነው ዝም አልልም" በሚል መሪ ቃል የነጭ ሪቫን ቀን ተከበሮ ዋለ::
"የሴት ጥቃት የኔም ነው ዝም አልልም" በሚል መሪ ቃል የነጭ ሪቫን ቀን ተከበሮ ዋለ::
17/04/2017
****አዲስ አበባ****
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የአለም የነጭ ሪቫን ቀን በዓለም ለ33 ጊዜ በሀገራችን ለ19 ጊዜ እንዲሁም የህፃናት ቀን በዓለም ለ35ኛ በሀገራችን ለ19ኛ ጊዜ በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተከብሮ ውሏል።
የሴት ልጅ ጥቃትን መከላከል ትውልድን ማፅናት ስለሆነ ሁሉም አካል በሴት ልጅ ላይ የሚደርስ ማንኛውንም ጥቃት የመከላከል ኃላፊነት አለበት ያሉት ከአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የተገኙት ወ/ሮ ራሄል ሙሉጌታ ናቸው።
"በተጨማሪም "ህፃናት የሚሉት አላቸው እናዳምጣቸው" በሚል መሪ ቃል የህፃናት ቀንንም የተመለከተ ሰነድ አቅርበዋል።
በሰነዱም ላይ ህፃናት ሀሳባቸውን በነፃነት እንዲገልፁ ማድረግ በራስ መተማመናቸው እንዲጨምር እና ችግር ፈቺ ሀሳብ አመንጪ ትውልድ እንዲፈጠር ትልቁን ሚና እንደሚጫወት አብራርተዋል።
በመጨረሻም ጤናማ እና የሚደመጥ ትውልድ ለማፍራት ሁሉም አካል የሚጠበቅበትን የቤት ስራ መወጣት ይገባል የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል::
ዘገባ :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments