
ባለስልጣኑ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የገና ስጦታ አበረከተ
ባለስልጣኑ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የገና ስጦታ አበረከተ
28/04/2015 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 ዓ.ም የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰራተኞቹና በደንብ ማስከበር ሂደት ጉዳት የደረሰባቸው አባላቱ የገና በዓል ስጦታ አበረከተ።
በበዓል ስጦታው ባለስልጣኑ ከ863,400 ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የዶሮ መግዣ የገንዘብ ስጦታ አበርክቷል።
በፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሰን በማለት መልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ አክለውም የከተማው ነዋሪ በሚኖሩበት አከባቢ ለተቸገሩ ጎረቤቶቻቸው መዓድ በማጋራት በዓሉን በመተሳሰብ እንዲያሳልፉ አደራ ብለዋል።
በዓሉን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የደንብ መተላለፎችን በመከላከልነሠ ተከስተቀ ሰመገኝ በነፃ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ በመስጠት በዓሉ በሠላም እንዲከበር ሁሉም ዜጋ የበኩሉን አስተዋፆኦ እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የበዓል ስጦታው በባለስልጣኑ የክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶች ለሚያሳድጓቸው ልጆችና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰራተኞቻቸው የተለያዮ የዓይነትና የገንዘብ የበዓል ስጦታዎች አበርክተዋል።
ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments