ባለስልጣኑ የአቅመ ደካማ ቤት አድሶ በማጠናቀቅ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የአቅመ ደካማ ቤት አድሶ በማጠናቀቅ ከበዓል ስጦታ ጋር ለባለቤቱ አስረከበ

ባለስልጣኑ የአቅመ ደካማ ቤት አድሶ በማጠናቀቅ ከበዓል ስጦታ ጋር ለባለቤቱ አስረከበ

                28 - 04 - 2017 ዓ.ም
                    ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በስሩ የሚገኙ ወረዳዎችን በማስተባበር በወረዳ 6 ለሚገኙ አቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት ሙሉ እድሳት አድርጎ በማጠናቀቅ ከበዓል ስጦታ ጋር ለባለቤቱ አስረከበ። 

በርክክብ ፕሮግራሙ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ ደንብ መተላለፎችንና ህገወጥ ተግባራትን ከመከላከል ጎንለጎን ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ ችግር ፈቺ የሆኑ ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ስራዎችን በመስራት ዛሬ እድሳቱ አጠናቆ ለርክክብ የበቃው ቤት አንዱ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይም ሰው ተኮር ተግባራት ተቋሙ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። 

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ ተስፋዬ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ በዋነኝነት የተሰጠንን ተልዕኮ ከማሳካት ባሻገር በተለያዩ  የበጎ ፈቃድ ተግባራት በመሳተፍ ላይ እንደሆነ ገልፀው በክ/ከተማው ወረዳ 6 ለሚገኙ አቅመ ደካማ የቤት እድሳት የወረዳውን አመራሮች በማስተባበር  በማጠናቀቅ በበዓል ዋዜማ ለባለቤቱ በማስረከባቸውን መደሰታቸው ገልጸዋል ። 

የቤቱ እድሳት የተደረገላቸው ወ/ሮ በቀለች ባልቻ ቤታቸው በመታደሱ እና በባለስልጣኑ በተደረገላቸው የማዕድ ማጋራት የደንብ ማስከበር ባለስልጣንን በተለይም የለሚ ኩራ  ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤትን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ በማስረከቡ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። 

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments