ባለስልጣኑ ከሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር የስድስት ወ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ከሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር የስድስት ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ

ባለስልጣኑ ከሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር የስድስት ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ

          01 - 05 - 2017 ዓ.ም
          **** አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት  የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸሙን የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ተገመገመ ። 

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ከባለስልጣኑ ጋር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ባከናወናቸው ውጤታማ ስራዎች በከተማዋ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ማስፈን አና በከተማው የሚታዪ የደንብ ጥሰትን በመከላከል ረገድ ውጤታማ ስራዎች መሠራታቸው ገልፀዋል።  

አክለውም ደንብ ማስከበር ራሱን በማዘመን ቢሮውን ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ ማድረግ መቻሉ የሚበረታታ መሆኑን የቢሮ ኃላፊዋ ገልጸዋል ። 

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት  ውጤታማ የሆኑ አፈፃፀሞች የተገኙት ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋቱ ስራዎችን በዕቅድ መሠረት ማከናወን በመቻሉ ነው።

አክለውም በግማሽ ዓመቱ ሳይከወኑ የቀሩና በክፍተት የታዩ ጉዳዮችን ዕቅድ በመከለስ የተሻለ ስራ ለማከናውን ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል። 

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ በዝርዝር ቀርቧል።

ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ እስከአሁን ባለው ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ወደ ፋይናንስ ገቢ ማስገባት መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል ። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮን የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሀብቴ ቀርቧል።

በሪፖርቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር በመስራት በከተማዋ ውስጥ ሠላምና ጸጥታን የሚያደፈርሱ አዝማሚያዎችን ቀድሞ በመለየት እና የተፈጸሙ ድርጊቶችን ሳይባባሱ በቅንጅት በመከላከል የከተማውን እና የህብረተሰቡን ደህንነት በማስጠበቅ ላይ መሆኑ ተገልጿል። 

በእለቱ ከሁለቱም ተቋማት ማኔጅመንት አባላት በቀረቡት ሪፓርት ዙሪያ በርካታ ሀሳብና አስተያየቶች ተነስተው የተንሸራሸሩ ሲሆን ስራዎችን ማዘመን ዲጅታል ማድረግ እና በቅንጅት የሚሰሩ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል የሚለው ሀሳብ ተነስቷል። 

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በግማሽ ዓመቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር ክፍተቶችን ደግሞ በመሙላትና በማረም ለተሻለ ውጤት ሁሉም አመራርና ፈፃሚዎችን በማስተባበር ለለውጥ እንዲተጋ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። 

ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments