ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥራዎችን ጉብኝት አደረገ

ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥራዎችን ጉብኝት አደረገ

                02 - 05 - 2017 ዓ.ም
             **** አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች እና ዳይሬክተሮች በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋናው መስሪያ ቤት በመገኘት የተቋሙ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መታገዝ የሚከናወኑ ሥራዎችን ተሞክሮዎች ወደ በተቋሙ  ለመተግበር ጉብኝት አድርገዋል። 

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለወንጀል መከላከልና ለወንጀል ምርመራ ሥራ የታጠቃቸውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አቅሞችን  በመጠቀም ስራዎችን ክትትል የሚደረግበት ስረዓት መመልከት ተችሏል ።

የፌደራል ፖሊስ ሪፎርም ተከትሎ በርካታ ተግባራትን በዲጂታል መንገድ እያከናወነ ይገኛል ከነዚህም ውስጥ የዜጎች ተሳትፎ ማረጋገጫ(EFP App) በተለያዩ የቋንቋ አማራጭ የቀረበ ለአጠቃቀም ቀላል ሆኖ የተለያዩ መረጃዎችን ህብረተሰቡ መጠቆም ሲፈልግ ባለበት ቦታ ሆኖ የተመለከተውን የወንጀል ድርጊት አዲስ በተከፈተው አፕሊኬሽን በመጠቀም የፎቶ፣ የቪዲዮ፣ የድምፅ መልእክቶችን በመላክ ለተቋሙ ተደራሽ ማድረግ የሚችልበት መንገድ   ገለፃ ተደርጓል።

በተጨማሪም ህብረተሰቡ በ991 ነጻ የስልክ  መስመር በመጠቀም ጥቆማዎችን መሰጥት እንደሚችል የፌደራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ ኮ/ር ደምስ ገልጸዋል ። 

የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተጠናከረ ኃይል ለመገንባት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተፈጠረው ሁለንተናዊ አቅም  በተለይም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀምና  በሎጂስቲክስ  አቅም ግንባታ ላይ እየታየ ያለው ከፍተኛ ለውጥ ለሌሎች ተቋማትም ሞዴል ሆኖ የሚያገለግል ነው  ብለዋል። 

አክለውም ከልምምድ ልውውጡ ያገኘነውን ተሞክሮና እውቀት ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሚያስፈልጉትን ተግባራዊ  ተናግረዋል ። 

ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments