
ከቃል እስከ ባህል በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሄደ
ከቃል እስከ ባህል በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሄደ
የፐብሊክና የፍትህ ልዩ ወረዳ አካል የሆነው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን መሠረታዊ ፖርቲ የ2ኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ቅድመ ጉባዔ ኮንፈረንስ ተካሄደ።
በመድረኩ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፐብሊክና የፍትህ ልዩ ወረዳ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሰፍ መብራቴ ለውጡ ከመጣ ጀምሮ ብዙ ይበል የሚያሰኙ ለውጦችን አይተናል ብለዋል።
በመጀመርያው ታሪካዊ ጉባኤ ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች በምን ያህል ስኬት እና ውጤት እንዳከናወናቸው እና የተመዘገቡ ስኬቶችን በማየት ፣ ቀሪ ስራዎችም በቀጣይ በተሻለ ውጤት ለማጠናቀቅ መነሳሳት የሚፈጠርበት ኮንፈረንስ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
በመድረኩን ንግግር ያደረጉት የደ/ማ/ባ የመሰረታዊ ፖርቲ አደረጃጀት ሰብሳቢ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በፖርቲው እየተገበረው የሚገኘው ሪፎርም በርካታ እንቅፍቶችን እየተሻገረ ድሎችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ከቃል እስከ ባህል የሚለው የውይይት ሰነድ፣ የኦዲት እና ኢንስፔክሽን ሪፖርት እና የፖርቲው የመተዳደሪያ ደንብ ቀርበው በሰነዶ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱ አብሮነትን በማጠናከር ፣ ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጎልበት፣ በጋራ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት ለተሻለ ስኬት ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያግዘው መሆኑ ተገልጿል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments