ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎችን የቅድመ መከላከል ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ እንደ ሚሰራ ገለፀ
ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎችን የቅድመ መከላከል ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ እንደ ሚሰራ ገለፀ
ጥር 09/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያ 6 ወራት የተሰሩ የደንብ መተላለፍ የቅድመ መከላከል ስራዎች፣ የተወሰዱ እርምጃዎች፣የሰው ተኮርና የልማት ስራዎችን አስመልክቶ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ ።
መድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት ባለፉት 6 ወራት ባለስልጣኑ የተሰጡትን ተልዕኮዎችን በአግባቡ የተወጣበት፣የተቋሙን አሰራር ለማዘመን በርካታ ሰራዎች የተሰሩበትን ፣ በተለይም የጎዳና ላይ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰበት እና በሁሉም የደንብ ጥሰቶች ውጤታማ ስራዎች የተሰሩበትን መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
አክለውም በከተማ አስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች በመጠበቅ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጥምር ግብረ ሀይል ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል ።
ዋና ስራ-አስኪያጁ በቀጣይ የደንብ መተላለፎችን እርምጃ ከመውሰድና ባሻገር የቅድመ መከላከል ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ እንደ ሚሰራ ገልጸዋል።
የባለስልጣኑ ስድስት ወራቱ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ የእቅድ በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።
በሪፖርቱም ታቅደው የተፈጸሙ ተግባራት ፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ችግሮችን ለመፍታት የተወሰዱ መፍትሔዎች ቀርበው የቀጣይ መፍትሄ ላይ ውይይትና የትኩረት አቅጣጫ ተሰቷል።
በሪፖርቱ ከተወረሱ ንብረቶችና ከጨረታ ሰነድ ሽያጭ ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ፋይናንስ ገቢ ማድረግ መቻሉን በሪፖርቱ ተገልጿል ።
በዕለቱ ተቋምን ከማዘመንና ዲጅታልላይዝ በማድረግ እሰከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ሊተገበር እንደሚገባ ከተሳተፊዎች ተጠቁሟል።
በቀረቡት ሪፓርት ዙሪያ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች በርካታ ሀሳብና አስተያየቶች ተነስተው በማዕከሉ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments