
የእንኳን ለ2017 ዓ.ም የጥምቀትና በዓል በሰላመ አደረሳችሁ!
የእንኳን ለ2017 ዓ.ም የጥምቀትና በዓል በሰላመ አደረሳችሁ!
ጥር 10/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሳችሁ እያለ፤በዓሉ የሠላም፣
የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱ ይገልፃል።
የጥምቀት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እምነታቸውን በነፃነት በአደባባይ ወጥተው በጋራ የሚያከብሩበት ፣የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክሩበት ፣መንፈሳዊ እሴቶቻቸውን የሚያዳብሩበት እና ማህበረሰባችን ተቻችሎና ተከባብሮ በጋራ መኖርን ለመላው የዓለም ህዝቦች ተምሳሌትነቱን የሚያሳዩበት ታላቅ በዓል ነው።
በዓሉ የአብሮነትና የሰላም በመሆኑ በዓሉ ስናከብር በጋራ፣በመተሳሰብ፣ በአንድነት የበዓሉን ሀይማኖታዊ ይዘቱንና ኢትዮጵያዊ ዕሴቶቻችንን በጠበቀ መልኩ ሊናከብረው ይገባል።
በዓሉ ስናከብር በከተማው የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች እና ተያያዥ ህገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈጸሙ፣የኮሪደር ልማት ስራዎች እንዳይበላሹ እና በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩልን ድርሻ እንዲወጣ አደራ ማለት እወዳለሁ፡፡
መልካም የጥምቀት በዓል !
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ዋና ሥራ-አስኪያጅ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments