ባለስልጣኑ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የደንብ ማስከበር አመራርና አባላት ገለፁ

ባለስልጣኑ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ  የደንብ ማስከበር አመራርና አባላት ገለፁ 

                  11/05/2017 ዓ.ም
                 **አዲስ አበባ** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማ አስተዳደሩ ከተሰጠው ተግባር እና ኃላፊነት በተጨማሪ በከተማው የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ። 

የባለስልጣኑ አመራርና አባላት በትናንትናው እና በዛሬው ዕለት እየተከበረ የሚገኘው የአደባባይ በዓል የሆነውን  የጥምቀት በዓልን በከፍተኛ ሁኔታ እያስተባበሩ እና የፀጥታ ሁኔታዎች ከሌሎች የፀጥታ ጥምር ሀይሎች ጋር በመሆን
እያስከበሩ መሆኑ አባላቱ ገልፀዋል።

በክብረ በዓሉ ከወላጆቻቸው የጠፍ ህፃናትን ከቤተሰቦቻቸው የማገናኘትና የምዕመኑን ስልክ በመስረቅ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ  በማድረግ ከፍተኛ አስተዎፆኦ እያበረከቱ መሆኑ ገልፀዋል። 

ዘገባው:- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments