ባለስልጣኑ በመጀመሪያው 6ወራት ከባለድርሻ ጋር...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በመጀመሪያው 6ወራት ከባለድርሻ ጋር በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ከ27 ተቋማት ጋር የአፈፃፀም ግምገማ እና የእውቅና መድረክ አካሄደ።

ባለስልጣኑ በመጀመሪያው 6ወራት ከባለድርሻ ጋር በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ከ27 ተቋማት ጋር የአፈፃፀም  ግምገማ እና የእውቅና መድረክ አካሄደ። 

               13/05/2017 ዓ.ም
                  ****አዳማ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው 6 ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም ለመገምገም በዛሬው ዕለት የከተማውና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ፣የተቋሙ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ የባለስለጣኑ አመራሮች በተገኙበት የአፈፃፀም  ግምገማ እና የእውቅና መድረክ አካሄደ። 

በመድረኩ  የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት ከተማችን አዲስ አበባ የበርካታ ዲፕሎማት ማረፊያ ናት፤ ተቋሙ ስሟ እና ተግባሯ ተመሳሳይ እንዲሆን እየሰራ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል። 

ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የደንብ መተላለፎችን የሚጠየፍ ህብረተሰብ ከመፍጠር አንፃር ውጤት እያስመዘገበ መሆኑ ገልፀዋል።

 ተቋሙ በህግ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራዎችን ለመስራት ጥረት እያደረገ እና የህግ ማስከበር ስራዎችን በማዘመን ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀው ሸስራው ዘላቂ እንዲሆን ተቋሙ ከተፈራረማቸው ተቋማት ጋር የተመዘገቡ እምርታዊ ውጤቶችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። 

በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር ሙሉነህ ደሳለኝ እንዳሉት የቅንጅት እና የትብብር አሰራር በድጋፍ ክትትል እንዲሁም በምዘና ወቅት ትኩረት እንዲሰጠው ማሳሰቢያዎችን እንሰጥ ነበር ሲሉ ተናግረው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመጀመሪያው ተቋም ነው ብለዋል። 

አክለውም በመናበብ የከተማችንን ነዋሪዎች የምናገለግል ልንሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። 

በዕለቱ የእንኳን ደና መጣቹ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት በ 2017 ዓ.ም  የ6ወራት የስራ አፈፃፀም በጋራ ከሰራናቸው 27 ባለድርሻ ተቋማት ጋር በመሆን የምንገመግም ይሆናል ብለዋል። 

በ6ወራት ውስጥ አብረን በሰራነው ልክ 56.8 የደንብ መተላለፎችን መቀነስ መቻሉን ገልፀው በቅንጅት በመስራት በርካታ ውጤቶችን ያስመዘገብን ሲሆን  ለዚህም በየጊዜው ተገናኝተን ውይይት ማድረግ በመቻላችን ነው በማለት  ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። 

በመቀጠልም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በ6ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀም በስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅትና አገልግሎት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ዳንኤል ቀፀላ ቀርቧል። 

በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የውይይት መድረኩን የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር ሙሉነህ ደሳለኝ እና የባስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከመድረኩ ለተነሱ ሀሳብ እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል። 

በመጨረሻም ከተቋሙ ጋር በጣም ከፍተኛ እና ከፍተኛ አፈፃፀም ላላቸው ባለድርሻ አካላት የእውቀና ሽልማት በተቋሙ ተበርክቶላቸው መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባው:-የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments