ባለስልጣናኑ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እና ከፋና...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣናኑ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እና ከፋና ቴሌቪዥን በጋራ ለመስራት የስምምነት ፊርማ ተፈራረመ

ባለስልጣናኑ  አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እና ከፋና ቴሌቪዥን በጋራ ለመስራት የስምምነት ፊርማ ተፈራረመ

                 16/05/2017 ዓ.ም
                ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የደንብ መተላለፎችን በተመለከተ የሚሰጠውን ግንዛቤ ለህብረተሰቡ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በቴሌቪዥንና በሬዲዮፕሮግራም እና በፋና ቴሌቪዥን በኦሮምኛ ቋንቋ ፕሮግራም  በጋራ ለመስራት የስምምነት ፊርማ ተፈራረመ ።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡን እያዝናና ግንዛቤ የሚፈጥሩ  ፕሮግራም በማዘጋጀት የባለስልጣኑ ተልዕኮ ፣ የደንብ መተላለፍ አይነቶችና ጉዳታቸው ፣ ደንብ መተላለፎችና ቅጣታቸው የተመለከቱ ፕሮግራሞች በአዲስ ሚዲያ በአማርኛና በፋና ቴሌቪዥን በኦሮምኛ ቋንቋ በሰፉ ሴራ ፕሮግራም  ለመስራት አቅዷል ።

በስምምነት ፊርማው የባለስልጣኑ አመራሮች ከተቋማቱ አመራሮችና ተወካዮች  በተገኙበት ተፈራርመዋል።

ዘገበው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments