ባለስልጣኑ የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ

ባለስልጣኑ የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ 

                  19/05 /2017 ዓ.ም
                 ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት አካሄደ፡፡ 

የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ  የእውቀት ሽግግር የተሞከሮ መድረክ በአመራሩና በሰራተኞች መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ተቀራርቦ ለመስራትና ለስራዎች ውጤታማነት  የሚያግዝ መሆኑ ገልፀዋል። 

በዕለቱ የባለስልጣኑ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ የራሳቸውን የህይወትና የትምህርት እና የስራ ተሞክሮና ልምዳቸውን ለሌሎች አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል። 

በእውቀት ሽግግር መድረኩ ሰራተኞች ስራቸውን አክብረው በመስራት በእውቀትና በክህሎት ራሳቸውን መገንባት እንዳለባቸው እና ተገልጋዮችን በቅንነት ማገልገል እንደሚገባቸው አቶ እዬብ ከበደ ተናግረዋል፡፡ 

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments