ባለስልጣኑ የተመደቡት አመራር ከተቋሙ አመራሮችና...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የተመደቡት አመራር ከተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ

ባለስልጣኑ የተመደቡት አመራር ከተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ 

             ጥር 19/2017 ዓ.ም
                 አዲስ አበባ
                          
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በምክትል ስራ-አስኪያጅ ማዕረግ የስልጠና እና የቅድመ መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ሆነው ወደ ተቋሙ የተመደቡት አቶ ንጋቱ ዳኛቸውን ከተቋሙ የማዕከልና የክፍ ለከተማ አመራሮች በተገኙበት ከመላው የባለስልጣኑ ሰራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ። 

በመድረኩ የቀድሞ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅነት ያገለገሉና አሁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የተሾሙት ኮማንደር አህመድ መሀመድን የሽኝት ፕሮግራም ተደርጓል።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ወደ ተቋሙ ተመድበው ለመጡት አቶ ንጋቱ ዳኛቸውን ወደ ተቋሙ እንኳን ደና መጡ በማለት ከተቋሙ ለተዘዋወሩት ኮ/ር አህመድ መሀመድን ለባለስልጣኑ ስኬት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበው መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

ተቋሙ ውስጥ ያለው አንድነት ለስራዎች መሳካት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በቆየሁበት ጊዜ መረዳት ችያለው በማለት ለተደረገኝ የሽኝት ፕሮግራም ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉ የቀድሞ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ የአሁኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሀመድ  ገልጸዋል ። 

በቀጣይ የተጀመሩ ስራዎችን ከአመራሩና ከሰራተኞ ጋር በጋራ በመሆን በማስቀጠልና በማከናወን ውጤታማ በመሆን የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተናግረዋል። 

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments