የደንብ መተላለፍ ክትትል ፣ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ የቀሪ ስድስት ወራት የተከለሰ እቅድ ውይይት አካሄደ
የደንብ መተላለፍ ክትትል ፣ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ የቀሪ ስድስት ወራት የተከለሰ እቅድ ውይይት አካሄደ
22/05 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፍ ክትትል ፣ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ከተወጣጡ የግብረ ሀይል ቡድን አስተባባሪ እና የቁጥጥር ኢንስፔክሽን አስተባባሪዎች ጋር የውይይት መድረክ በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል ።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፍ ክትትል ፣ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2017 በጀት ዓመት የተከለሰ አቅድ በየደንብ መተላለፍ ክትትል ፣ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል አቅርበዋል ።
በመድረኩ ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ በመናበብ እየሰራ እንደሚገኝና በዚህም የተሻለ አፈጻጸም ማስመዘገቡንና በቀጣይም ይህን በማጠናከር የተሻለ ስራዎችን መስራት አንደሚገባ ተገልጿል ።
በሪፖርቱ ታቅደው የተፈጸሙ ክንውኖች ፣ ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራቶች ፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተከናወኑ መፍትሔዎች ተካተውበታል።
በባለስልጣኑ ግብረ ሀይል ቡድን እና በውስጥ ኦዲተሮች በተዋቀረ ኮሚቴ በ2017 በጀት ዓመት አስከ ህዳር 18 በአስራ አንዱም ክ/ከተማ ከጨረታ ሽያጭና ከቅጣት የተሰበሰበ ገንዘብ መጠን ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ የተሰሩ ሰራዎች ሪፖርት እና የከተማ አስተዳደሩና የባለስልጣኑ ንብረት ስለመያዝ ፣አሻሻጥና አወጋገድ ደንብና መመሪያ በባለስልጣኑ የግብረ ሀይል ቡድን መሪ አቶ ተሾመ ታደለ ቀርቧል።
የመድረኩ ዋና ዓላማ በአፈፃፀም ሂደት የታዩ ጥንካሬዎች፣ ድክመቶችና የአፈፃፀም ማነቆዎችን በመለየት የመፈጸምና የማስፈፀም አቅምን በማጎልበት ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት ለመፍጠር እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል ።
በመጨረሻም በቀረቡት ሪፖርቶች እና ሰነዶች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ሰፊ ውየይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል ።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments