ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎችን በካሜራና በመገና...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎችን በካሜራና በመገናኛ ራዲዮ በመታገዝ የቅድመ መከላከልና የቁጥጥር ስራ እንደሚጀመር ተገለፀ

ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎችን በካሜራና በመገናኛ ራዲዮ በመታገዝ የቅድመ መከላከልና የቁጥጥር ስራ እንደሚጀመር ተገለፀ

                23/05 /2017 ዓ.ም
                 ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በቴክኖሎጂ የታገዘ ስማርት ቢሮ ለመስራት የሁለቱ ተቋማት አመራሮችና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የከተማችንን ፈጣን እድገት ጋር የዘመነ የደንብ ጥሰቶችንና ህገወጥ ተግባራት የመከላከል ስራ ለማከናወን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትግበራ ለማድረግና ወደ ተግባር ለመግባትና የሚያስፈልጉ ግባአቶቸን በማሟላት ሰራዎችን ለመጀመር እቅድ ተዘጋጅቶ እንቅስቃሴ መጀመሩ ገልጸዋል ። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ የማነ ደሳለኝ በቴክኖሎጂ ተቋሙ ለማዘመን፣ ወጪን ለመቀነስ፣ እና አገልግሎት ለማሻሻል የሚረዱ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም የሚረዱ ፋይል ማኔጅመንት፣ ስማርት ኦፊስ፣ፊልድ ማኔጅመንት፣አሴት ማኔጅመንት እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች ለመዘርጋት ስራዎች መጀመራቸው ተናግረዋል ።

አክለውም ቢሮው ከባለስልጣናኑ ጋር በመተባበር ለስራው መሳካት የሚያስፈልጉ የሰው ሃይሉን በማብቃትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ሰፊ በማድረግ ተቋሙን ስማርት ቢሮ ለማድረግ በቀጣይም በሙሉ አቅም በማገዝ እንደሚሰራ ተናግረዋል ። 

ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎችን በካሜራና በመገናኛ ራዲዮ በመጠቀም መረጃ መሠረት  በማድረግ የቅድመ መከላከልና የቁጥጥር ስራ እንደሚጀመር ተጠቁሟል። 

ቴክኖሎጂው መሳሪያዎች እና ስርዓቶች የደህንነት እና የግንኙነት ስርዓቶች በማሻሻል በተቋማት ውስጥ የሚገኙ የግንኙነት ስርዓቶች በቪዲዮ ኮንፈረንስ በመደገፍ አገልግሎትን ለማሻሻል እንደሚረዳ በውይይቱ መድረኩ ተገልጿል ። 

በመጨረሻም ለስራው መሳካት በተነሱ ሀሳቦች ላይ ውይይት ተካሂዶ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ በፍጥነት ተግባራዊ ለማድረግ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ። 

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments