"የምንሰጠው አገልግሎት በቅንነትና በፍትሀዊነት...

image description
- In code inforcement    0

"የምንሰጠው አገልግሎት በቅንነትና በፍትሀዊነት ከብልሹ አሰራርና ከሙስና የጸዳ ሊሆን ይገባል" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለሥልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ

"የምንሰጠው አገልግሎት በቅንነትና በፍትሀዊነት ከብልሹ አሰራርና ከሙስና የጸዳ ሊሆን ይገባል" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለሥልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ
            
                  24/05 /2017 ዓ.ም
                ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት  "ስነምግባርና መልካም አስተዳደር ለተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ " በሚል መሪ ቃል የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የአንደኛ ዙር ስልጠና ተሰጠ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለሥልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተቋም ግንባታ ስራችንን ስናከናውን ስነ-ምግባርን  በመላበስ የሚጠበቅብንን ሙያዊ ኃላፊነት በአግባቡ መውጣትና ስራዎችን ሰንሰራና ህብረተሰቡን ስናገለግል  በቅንነት፣በፍትሀዊነት እና በቅልጥፍና አገለግሎት በመስጠትና ሁሉም አካል ራሱን ከብልሹ አሰራርና ከሙስና የጸዳ በማድረግ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ 

አክለውም በከተሞችን እየተከናወነ የሚገኙት የኮሪደር ልማት ስራዎች ላይ ኦፊሰሩ ከአመራሩ የሚሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት ያለውን አቅም ያሳየበትና በከተማ ደረጃ ተቋማችን እውቅና ያገኘበት መሆኑንና በቀጣይም ተጠናክሮ ሊሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ። 

በመድረኩን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ ተስፋዬ ባለፋት ስድስት ወራት እንደ ተቋም በተሰጠን ተልዕኮ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎቻችን በማጠናከር ህብረተሰቡ ከደንብ መተላለፍ ቅጣት  አንዲጠበቅና ህገወጥነትን እንዲጸየፍ የማድረግ ስራ እያከናወነ አልፎ የሚመጡትን ደንብ ተላላፊዎች በመከላከል በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ በክ/ከተማው የሚታይ የነበሩ ደንብ ጥሰቶችን 60% መቀነስ መቻሉን ገልጸዋል ።

በግማሽ ዓመቱ በክፍለ ከተማው ከአራት ሺ በላይ ደንብ ተላላፊዎችን በመቅጣት ከ20ሚሊዮን ብር በላይ ለፋይናንስ ገቢ ማድረግ መቻሉን ኃላፊው ገልፀዋል ።

በተጨማሪም ከተሰጠው ተልዕኮ ጎን ለጎን የበጎ ፍቃድ ሰው ተኮር ሰራዎችን በማከናወን ወላጅ አልባ ህጻናትን መንከባከብና መደረገፍ እንዲሁም ሁለት የአቅመ ደካማ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቱ ማስረከባቸውን ኃላፊው ተናግረዋል። 

የስነምግባርና መልካም አስተዳደር ብልሹ አሰራርን ቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል የተዘጋጀው የግምገማዊ ስልጠና ሰነድ በባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል። 

የስነምግባርና ብልሹ አሰራር ችግር ለተቋማችን ገጽታ ግንባታ ያለውን ተጽዕኖ በመገንዘብ በዚህ ድርጊት የሚሳተፉትን ጠንካራ የተጠያቂነት ስርዓት መዘርጋትና ሁሉም አካል ብልሹ አሰራርን ሊታገለው እንደሚያስፈልግ አቶ እዬብ ከበደ ገልጸዋል ። 

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት ቀጣይ የስራ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ ተስፋዬ ተሰጥቶበታል ስልጠናው በሁለተኛ ዙር ለቀሩት ኦፊሰሮች በነገው ዕለት እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችለል ።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments