
የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡና የአደባባይ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅናና የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ
የየተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡና የአደባባይ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅናና የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ
24/05/2017ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም በመጀመሪያ ግማሽ አመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡና የአደባባይ በዓላት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስተዋፅኦ ላበረከቱ ለባለድርሻ አካላት እና የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ወረዳዎችና የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች እውቅናና የምስጋና ፕሮግራም የባለስልጣኑና የክፍለ ከተማው አመራሮች በተገኙበት የእውቅናና ምስጋና እና ፕሮግራም ተካሂዷል።
በመረሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈሪ እንደገለፁት፣ የባለስልጣኑን የውስጥ አሰራሮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው አመራሩና ኦፊሰሩ በሰራው ጠንካራ ስራ የደንብ ጥሰት ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር በከተማዋ 58 በመቶ ቀንሷል ብለዋል።
ተቋሙን በቴክኖሎጂ፣ በሰው ሀይል እና በአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ናቸው።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊ ኮማንደር ግርማ ሰንበቱ በበኩላቸው የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም በመጀመሪያ ግማሽ አመት ከ6 ሚሊየን ብር በላይ በቅጣት እና በጨረታ ገቢ ማድረጉን ገልፀው ባሳለፍነው አመት ተመሳሳይ ወቅት የተገኘው 3 ሚሊዮን ብር እንደነበር አስታውሰዋል።
ሀላፊው በተያዘው በጀት አመቱ 6ወራት የደንብ መተላለፎች በብቃት በመከላከል እና በመቆጣጠር የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ወረዳዎች እና የተከበሩ በአላትን/የኢሬቻ፣ መስቀል እና ጥምቀት/ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲያልቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለ ድርሻ አካላት እና የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች እውቅና መስጠት የቀጣይ ስራችን ላይ ተነሳሽነት እንደሚፈጥር ገልጿል።
በእውቅና እና ሽልማቱን ፕሮግራሙ ወረዳ1፣ወረዳ10 እና ወረዳ 8 ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ዘገባው:-የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments