
ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ።
ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ።
26-05 -2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም ተካሄደ
የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ንቁ በሆነ መንፈስ ሳምንቱን በጥሩ ሁኔታ ዉጤታማ ስራ ለማከናወንና በየሳምንቱ ከሰራተኞቻችን ጋር እንደቤተሰብ እየተማማርን እና እየተመካከርን ሳምንቱ ሙሉ ወርቃማ እንዲሆንልን መልካም ምኞት በመለዋወጥ እርስ በእርሳችን የምንመካከርበት፣ የምንማማርበት፣ ልምድ የምንለዋወጥበት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል ።
በዕለቱ የባለስልጣኑ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላቀች ሀይሌ የራሳቸውን የህይወትና የትምህርት እና የስራ ተሞክሮና ልምዳቸውን ለሌሎች አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል።
ራስን ሁል ጊዜ በዕውቀት ማዳበር ፣ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ጋር መልካም ግንኙኘት መኖር ፣ለባለሙያ ልምድን ማጋራት እና ስራን በትብብር ፣ በአንድነት እና ዝቅ ብሎ መስራት ዉጤታማ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ወ/ሮ ላቀች ሀይሌ በአብሮነት በመተባበር እንደዚህ ቆሜ እንድናገር ላበቁኝ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞች ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments