
ባለስልጣኑ ለ6ኛ ዙር አዲስ እጩ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የምልመላ መስፈርቱን የምልመላ ሂደቱን በተመለከተ ውይይት አካሄደ
ባለስልጣኑ ለ6ኛ ዙር አዲስ እጩ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የምልመላ መስፈርቱን የምልመላ ሂደቱን በተመለከተ ውይይት አካሄደ
ጥር 26/2017 ዓ.ም
****የአዲስአበባ****
የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለ6ኛ ዙር ሁለት ሺህ እጩ ኦፊሰሮችን መልምሎ የንድፈ ሀሳብና ወታደራዊት ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ ለማሰማራት የምልመላ መስፈርቱን የምልመላ ሂደቱን በተመለከተ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ።
የአዲስ የአኦፊሰሮች ምልመላው ባለስልጣኑ የከተማች የደንብ መተላለፎች ከመከላከል፤ መቆጣጠርና እረምጃ ለመውሰድ የከተማችን የልማት ኮሪደር ለማስጠቅ መሆኑን የባለስላጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አስታውቀዋል፡፡
የእጩ ኦፊሰሮችን ምልመላው የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሳደግ የታቀደ መሆኑን ተገልጿል፡፡
ምልመላው ፍታዊ እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጽጥታ ቢሮ ፤ፐፕሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል አስተዳደር ቢሮ ፤ጤና ቢሮ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኮሚቴ አባልነት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተነግሯል ፡፡
የ6ኛ ዙር ምልመላ ሲደረግ ታሳቢ የሚሆነው በትምህርት ዝግጅታቸው ድጊርና ከዛበላይ እንዲሁም ሁለንተናዊ ስእብናቸው ንቁና ብቃት ያላቸው እጩ የሰው ኃይል እንደሚመለምል ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
በውይይት መድረኩ የክፍለ ከተማና የወረዳደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች የምልመላ ሂደቱንና ተጨማሪ ሊካተቱ የሚገቡ መስፈርቶችን በተመለከተ ሀሳብና ጥያቄዎች በማንሳት ከበላይ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሠጥቷል።
በመጨረሻም የምዝገባ ቀናትና ዝርዝር የምልመላ መስፈርቶች በቀጣይ ለስራ ፈላጊዋች በሚዲያ እንደሚገለፅ ተመላክቷል።
ዘገባው፦ የአዲስአበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments