ባለስልጣኑ የቀሪ ስድሰት ወራት የተከለሰ የእቅድ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የቀሪ ስድሰት ወራት የተከለሰ የእቅድ ውይይት አካሄደ

ባለስልጣኑ የቀሪ ስድሰት ወራት የተከለሰ የእቅድ ውይይት አካሄደ 

           26-05 -2017 ዓ.ም
           ****አዲስ አበባ**** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ ስድስት ወራት የተከለሰ ዕቅድ ውይይት ከማዕከሉ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ ። 

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለሥልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ባለፈው ስድስት ወራት በነበረን አፈፃፀም  የታዩ ጥንካሬዎች በማስቀጠል  የታዩ ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ ወራት የመፈጸምና የማስፈፀም አቅምን በማጎልበት  ውጤታማ ውጤታማ ተግባር መከናወን ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል ። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2017 በጀት ዓመት የጣይ ስድስት ወራት የተከለሰ እቅድ ሰነድ በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል ።

በሰነዱ ባለፉት ስድስት ወራት የተቋም ግንባታ ፣የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፋት መስራት እና በከተማዋ የሚታዪ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ህጋማዊ እርምጃ መወሰዱን ተጠቅሰዋል፡፡

ባለስልጣኑ ከተሰጠው ተልዕኮ ጎን ለጎን የበጎ ፍቃድ ሰው ተኮር ሰራዎችን በማከናወን አስራ አንድ የአቅመ ደካማ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ ማስረከቡ በሪፖርቱ ተገልጿል ። 

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ። 

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments