የደንብ ማስከበር ተልዕኮን ለማስፈፀም በስነ-ምግ...

image description
- In code inforcement    0

የደንብ ማስከበር ተልዕኮን ለማስፈፀም በስነ-ምግባር የታነፀ ኦፊሰርን መገንባት እንደሚገባ ተገለፀ።

የደንብ ማስከበር ተልዕኮን ለማስፈፀም በስነ-ምግባር የታነፀ ኦፊሰርን መገንባት እንደሚገባ ተገለፀ።

27/05/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት በስነ-ምግባር የታነፀ እና ሌብነትን የሚፀየፍ ኦፊሰርን ለማብቃት የሚያስችል ግምገማዊ ስልጠና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አዳራሽ አካሄደ።

በግምገማዊ ስልጠናው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሁሉም ወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማው የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ቡድን መሪ፣ ተባባሪ አካላትና አጠቃላይ ኦፊሰሮች ተካፋይ ሆነዋል።

መድረኩን ያስጀመሩት የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ ዓለሙ እንደተናገሩት ኦፊሰሩን ለተልዕኮ ዝግጁ ለማድረግ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ ለማብቃት እየተሠራ እንደሚገኝና ውጤታማ ስራዎችንም ማከናወን እየተቻለ መሆኑን ገልፀዋል።

የመድረኩ የክብር እንግዳ የሆኑት የክፍለ ከተማው ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ በቀለ እንዳሉት ተቋሙ ከጊዜ ወደጊዜ እራሱን በማዘመን የደንብ መተላለፎችንና የፀጥታ ስራዎችን በብቃት በመወጣት ተልዕኮውን እየፈፀመ እንደሚገኝና በቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ግምገማዊ ስልጠናውን የሰጡት እና የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ሲሆኑ ስነ-ምግባርና ብልሹ አሠራርን ከመልካም አስተዳደር አንፃር በመቃኘት ለችግሩ መፍትሔ ማስቀመጥና ተጠያቂነትን ማስፈን የስልጠናው ዓላማ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በመሆኑም ባለስልጣኑ ፈፃሚውንና ኦፊሰሩን ከስነ-ምግባርና ብልሹ አሠራር እራሱን በመጠበቅ የከተማ አስተዳደሩን ተልዕኮ ከዳር እንዲያደርስ የተለያዩ የአቅም ግንባታ እና ግምገማዊ ስልጠናዎችን እየሠጠ እንደሚገኝና በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በስልጠናው ያነጋገርናቸው  ሠልጣኞች እንደገለፁት፦ ማህበረሰቡን በመልካም ስነ-ምግባር በማገልገል ዘላቂ አጋርነቱን ማረጋገጥ እንድንችል ስልጠናው በርካታ ግንዛቤዎችን ያስገነዘበ መሆኑን አስረድተዋል።

የመድረኩን ውይይት የመሩት የክፍለ ከተማው  የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቱ ደሴ እንደተናገሩት የደንብ ማስከበር ኦፊሰር በህዝቡ ተመልምሎ ሠልጥኖ መልሶ ህዝቡን የሚያገለግል በመሆኑ ሁልጊዜ እራሱን ከብልሹ አሠራር እየጠበቀ ህብረተሰቡን በታማኝነት ሊያገለግል እንደሚገባ ተናግረዋል።

አክለውም በከተማዋ ውስጥ ያለውን ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ስራዎች የተሳለጡ እንዲሆኑ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሩ ሚና የላቀ በመሆኑ በቀጣይም በትጋት ተልዕኮውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments