
የስራ ቅጥር ማሰታወቂያ
የስራ ቅጥር ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር አዋጅ ቁጥር 84/2016 መሰረት የደንብ ማስከበር ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን በምልመላ መስፈርቶች መሰረት አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡
ሀ) አጠቃላይ የምልመላ መስፈርቶች
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት የተቀበሉ፣ በህዝቦች ሉአላዊነትና አንድነት የሚያምኑና አገራቸዉን ለማገልገል ሙሉ ፍቃደኛ የሆኑ፤
ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች ወገንተኝነት ነፃ የሆኑ፤
ከአሁን በፊት የመከላከያ፣ የፖሊስ፣ የክልል ልዩ ሃይል እና ደንብ ማስከበር አባል ያልነበሩ፤
በወንጀል ይሁን በፍታብሔር ተከሶ የፍርድ ቤት ክርክር የሌለባቸው፣
ዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች፤
መሰረታዊ የፓራሚሊተሪ ስልጠና ወስደው ከተመረቁ በኋላ ለ5 አመት ለማገልገል ውል ለመፈፀም ፍቃደኛ የሆኑ፤ እና ቢሮዉ የሚያዘጋጀዉ የስራ ዩኒፎርም ለመልበስ ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች
በደንብ ማስከበር ባለስልጣን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት መብትና ግዴታቸውን አውቀው በየትኛዉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ተመድቦ ለማገልገል ፍቃደኛ የሆኑ፤
በተቋሙ የሚሰጣቸውን ስልጠናዎች ለመሰልጠን ፍቃደኛ የሆኑ እና ከየትኛዉም ሱሶች (ከሲጋራ፣ከጫት፣ ከሀሽሽ እና ከሌሎች ሱሶች ነፃ የሆኑ)፤
በአካባቢው ማህበረሰብ የተመሰገነ ባሀሪ እና ስነ-ምግባር ያላቸው፤
ከተለያዩ ወንጀሎችና ፀረ-ህዝብ ተግባር ነፃ ስለመሆናቸው ከፈዴራል ፖሊስ የአሻራ ማሰረጃ እና የብሔራዊ መታወቂያ ማቅረብ የሚችሉ፤
ትዳር ያልመሰረቱና ልጅ ያልወለዱ፤
ዕድሜ ለሁለቱም ፆታ ተመልማዮች ከ18 እስከ 28 ዓመት የሆኑ(የ8ኛ ክፍል ሚንስትሪ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ)፤
በማንኛዉም የትምህርት መስክ ዲግሪና ከዚያ በላይ የሆኑ
ሙሉ ጤንነት ያላቸውና ስልጠናው የሚጠይቀውን የህክምና ምርመራ ለማድረግ ፍቃደኛ የሆኑና በምርመራው ማለፍ የሚችሉ፤(የአይን፣ የአፍንጫ፣ የጆሮ፣ የጥርስ እና የከንፈር መሰንጠቅ ችግር የሌለባቸው፤ እንዲሁም ከቲቪ፣ ከሚጥል በሽታ፣ ከስኳር፣ ከደም ግፊት፣ ከኪንታሮት እና ከእንቅርት በሽታዎች ነፃ የሆኑ፤)
ለ. አካላዊ መስፈርት
1. የተስተካከለ ቁመና የእግር፣ የእጅ፣ የአንገት፣ የወገብ መሰበር እና ሌሎችም ችግሮች የሌለባቸው፤
2.ቁመት ለወንድ 1.60 ለሴት 1.55 ሜትር እና ከዚያ በላይ የሆኑ፤ ክብደት ለወንድ ከ45-70 ለሴት ከ 40-60 ኪ.ግራም የሆኑ፤
ማሳሰቢያ፡-
የሚቀርቡ የትምህርት ማስረጃዎች እውቅና ካለው የትምህርት ተቋማት የተገኙ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ---- ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወረዳችሁ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
በወረዳችሁ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ምልመላውን ያሟሉ ሰልጣኞች የህክምና ምርመራ እና ስልጠና የሚሰጥበት ጊዜ በተመዘገባችሁበት ተቋም በማስታወቂያ እና በስልክ ይገለጻል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments