ባለስልጣኑ በክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ሲያካሄድ የቆየውን የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ
ባለስልጣኑ በክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ሲያካሄድ የቆየውን የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ
04/06/2017 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በወረዳዎችና በክፍለ በከተሞች ሲካሄድ የቆየው የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራት ለመከላከል ያለመ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ማጠቃለያ ፕሮግራም ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ከተወጣጡ የከተማው ነዋሪዎች ጋር የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በጉለሌ ክ/ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከእቅድ አንፃር የተከናወኑ በርካታ የደንብ መተላለፎችን የመከላከል እና የመቆጣጠር ተግባራት እንዳሉ ጠቅሰው እነዚህ ተግባራት በህብረተሰቡ ተሳትፎ እና በባለድርሻ አካላት ትብብር የታገዙ እንደነበርና በቀጣይ ቀሪ ወራቶችንም ህብረተሰቡ ከጎናችን በመቆም በጋራ ሆነን ደንብ መተላለፎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል ።
አክለውም በተሰጠን ተልዕኮ ዘጠኙ የደንብ መተላለፎችን በመከታተል እና በመቆጣጠር በህጋዊ መንገድ የሚሰራውን ማህበረሰባችን በአግባቡ በማገልገል እየተከናወነ ያለውን የሪፎርም ስራዎቻችንን በማጠናከርና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራዎችን በማከናወን ከመቼውም ጊዜ በላይ ህብረተሰቡን ለማገልገል ዝግጁ መሆንናቸውን ገልፀዋል።
በመድረኩ የባለሥልጣኑ የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የተቋሙ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ አቅርበዋል ።
በሪፖርቱ ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በቁርጠኝነት ከመወጣት ጎን ለጎን ወደ ህብረተሰቡ በመውረድ ሰው ተኮር ስራዎችን በመከናወን በግማሽ ዓመቱ 11 የአቅመ ደካማ ቤቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ አስረክቦል፣ የአረንጓዴ አሻራ ተግባራት በማካሄድ ችግኞችን መትከልና መንከባከብ ስራ ተከናውኗል እንዲሁም ወላጅ አልባ ህጻናት በመንከባከብ እያሳደገ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
በተጨማሪም በመድረኩ የባለስልጣኑ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የመልካም አስተዳደር ብልሹ አሰራር አፈጻጸም ሪፖርት እና በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 167/2016 ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቧል።
በመጨረሻም በቀረቡት ሪፖርት እና ሰነዶች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል ።
ዘገባው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments