Events

In ደንብ ማስከበር ባለስልጣን

image description
Start Date icon
End Date icon
Location የቦሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት

የቦሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት የተከናወኑ አበይት ተግባራትን የሚያሳይ የፎቶ አውደ-ርዕይ በመገናኛ ዋና አደባባይ በማዘጋጀት ለ ለማህበረሰቡ ለዕይታ አቅርቧል።

በዕለቱ ከፎቶ አውደ-ርዕይ በተጨማሪ በሞንታርቦ የታገዘ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ በክ/ከተማው አደባባዮች በመኪና በመዘዋወር በድምፅ እና በበራሪ ወረቀትና በብሮሸር የታገዘ የግንዛቤ ማስጨበጥ ተግባር አከናውኗል።

በአውደ-ርዕዩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቦሌ ክ/ከተማ ጽ/ቤቱ ኃላፊ ኮ/ር አስፋው የሺዳኝ እንደተናገሩት ጽ/ቤቱ በአዋጅ የተሰጠውን ደንብን የማስከበር ተልዕኮ ከመወጣት ባሻገር ያከናወናቸውን ዋና ዋና ስራዎች በምስል አስደግፎ ለሚያገለግለው ህብረተሰብ ለዕይታ ማቅረብ መቻሉ ስራችንን ህዝባዊ ለማድረግ ያግዛል ሲሉ ተናግረዋል።

ህበረተሰቡ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የቅድመ መከላከል ሰራችንን በማጠናከር ከፎቶ አውደ-ርእይ በተጨማሪ በየጊዜው ሰለ ደንብ መተላለፎች በብሮሸር፣ በበራሪ ወረቀት እና በሞንታርቦ በክ/ከተማው በመዘዋወር የግንዛቤ ማስጨበጥ ሰራ እየተሰራ እንደሚገኝ ኃላፊው ገልጸዋል ።

የፎቶ አውደ-ርዕዩ ተሳታፊዎች ባዩት ነገር ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ደንብ ማስከበር አየሰራ ያለው ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

  • icon 9:30am - 1:00pm
  • የቦሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት

Related Events

image description
ደንብ ማስከበር ባለስልጣን

  • የቦሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
More Details