የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ም/ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ
Deputy manager of Authority:
ኮማንደር አህመድ መሃመድ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማከበር ባለስልጣን የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዘርፍ መልዕክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በኣዋጅ 74/2014 ባለስልጣን ሆኖ ከተደራጀ በኃሏ ተቋሙን ሪፎርም በማድረግ ከፍተኛ ስራዎችን እያሰራ ያለ ስሆን፣ በያዝነው በጀት ዓመትም የከተማ አስተዳደሩ አሰፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማቋቋም ባወጣው አዋጅ 84/2016 አንቀፅ 50 ላይ ተጠናክሮ ታውጃል፡፡ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዋጅ የተሰጡትን ኃላፊነቶች ለመወጣት "በ2022 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ እንዲሁም ለአፍርካ ከተሞች ተምሳሌት ሆኖ መየትን" ራዕይ ያነገበ ስሆን፣ ይህንን ራዕይ ለማስከትም "በህብረተሰቡ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ የደንብ መተላለፎችንና ተያያዥ ህገወጥ ተግባራትን በመከላከል፣ በመቆጣጠር እና እርምጃ በመውሰድ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ማራኪና ሰላማዊ እንዲትሆን ማድረግን" ተልዕኮ ይዛዋል፡፡ ይህንን ራዕይና ተልኮን በተገቢው ለማስከት እንዲረዳ ባለስልጣኑ ካሉት ሁለት ዓላማ ፈፃሚ ዘርፎች ውስጥ አንደኛው የስልጣናና የቅድመ መከላከል ዘርፍ ስሆን፤ ይህ ዘርፍም ራዕይውን ለማሳካትና ተልኮውን በአግባቡ ለመፈጸም እንዲረዳ ክፍተቶችን በመዳሰስ የውስጥ አቅምን ለማጎልበት የሚያግዝ የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን በመስጠት በየደረጃው ያለው አመራርና ፈጻሚ አካል በእውቀት ላይ የተመሰረተ አገልጋይ እንዲሆን ያለሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም ህብረተሰቡን በተለያየ አግባቦች በማሳተፍ ስለባለስልጣኑ አዋጅ፣ደንብና መመርያዎች ግንዛቤ እንዲኖረው፣ የደንብ መተላለፎችና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራትን እንዲፅየፍና በየደረጃው ከተሰማሩ የባለስልጣኑ አመራሮችና ኦፊሰሮች ጋር በመተባበር በህብረተሰቡ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ የደንብ መተላለፍ ደርግቶች እንዳይፈጸሙ አስቀድሞ በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መንገዶች በመጠቀም ለሁብረተሰቡ ግንዛቤ በመስጠት ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ከተማችን አዲስ አበባ የደንብ መተላለፎችና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራት የቀነሰባትና ለነዋሪዎቿ ምቹና ሰላማዊ እንዲትሆን እያደረግን ባለው ጥረት፣ ሁሉን አቀፍ የህብረተስብ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ከጎናችን በመሰለፍ ራዕይና ተልካችንን በጋራ እንዲናሳካ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የደንብ መተላለፎችን በጋራ እንከላከል!!!
Directorates under the sector:
ደንብ መተላለፍ ክትትል፣ ቁጥጥር፣ እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማከበር...
iconስልጠናና ጥናት ዳሬክቶሬት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማከበር...
iconደንብ መተላለፍ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማከበር...
icon